-
ዘፍጥረት 17:10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 እናንተም ሆናችሁ ከእናንተ በኋላ የሚመጡት ዘሮቻችሁ ልትጠብቁት የሚገባው በእኔና በእናንተ መካከል ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው፦ በእናንተ መካከል ያለ ወንድ ሁሉ መገረዝ አለበት።+
-
-
ዘፍጥረት 17:23አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 ከዚያም አብርሃም ልጁን እስማኤልን፣ በቤቱ የተወለዱትንና በገንዘቡ የገዛቸውን ወንዶች ሁሉ እንዲሁም በአብርሃም ቤት የሚገኙትን ወንዶች ሁሉ ወስዶ ልክ አምላክ በነገረው መሠረት በዚያኑ ዕለት ሸለፈታቸውን ገረዘ።+
-
-
ዘፍጥረት 22:3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 ስለዚህ አብርሃም በማለዳ ተነስቶ አህያውን ከጫነ በኋላ ከአገልጋዮቹ መካከል ሁለቱን ከልጁ ከይስሐቅ ጋር ይዞ ለመሄድ ተነሳ። ለሚቃጠል መባ የሚሆን እንጨትም ፈለጠ፤ ከዚያም ተነስቶ እውነተኛው አምላክ ወዳሳየው ስፍራ ተጓዘ።
-