የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 28:14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ዘርህም በእርግጥ እንደ ምድር አፈር ብዙ ይሆናል፤+ ወደ ምዕራብ፣ ወደ ምሥራቅ፣ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ትስፋፋለህ። የምድር ቤተሰቦች ሁሉ በአንተና በዘርህ አማካኝነት በእርግጥ ይባረካሉ።*+

  • ዘፍጥረት 46:2, 3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 2 ከዚያም አምላክ ለእስራኤል ሌሊት በራእይ ተገልጦለት “ያዕቆብ፣ ያዕቆብ!” ሲል ጠራው፤ እሱም “አቤት!” አለ። 3 አምላክም እንዲህ አለው፦ “እኔ የአባትህ አምላክ የሆንኩት እውነተኛው አምላክ ነኝ።+ ወደ ግብፅ ለመውረድ አትፍራ፤ ምክንያቱም በዚያ ታላቅ ብሔር አደርግሃለሁ።+

  • ዘፀአት 1:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 እስራኤላውያንም* ተዋለዱ፤ በጣም ብዙ ሆኑ፤ ቁጥራቸውም በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረና ኃያል እየሆኑ ሄዱ፤ ከዚህም የተነሳ ምድሪቱን ሞሏት።+

  • ዘፀአት 32:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ‘ዘራችሁን በሰማያት ላይ እንዳሉት ከዋክብት አበዛዋለሁ፤+ ለዘላለም ርስት አድርጎ እንዲወርሰውም ለዘራችሁ ለመስጠት ያሰብኩትን ይህን ምድር በሙሉ እሰጠዋለሁ’+ በማለት በራስህ የማልክላቸውን አገልጋዮችህን አብርሃምን፣ ይስሐቅንና እስራኤልን አስታውስ።”

  • የሐዋርያት ሥራ 7:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 “አምላክ ለአብርሃም የተናገረው የተስፋ ቃል የሚፈጸምበት ጊዜ ሲቃረብ ሕዝባችን በግብፅ እየበዛና እየተበራከተ ሄደ፤

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ