ዘፍጥረት 31:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 በዚህ ጊዜ ላባ በጎቹን ለመሸለት ሄዶ ነበር፤ ራሔልም የአባቷን+ የተራፊም ቅርጻ ቅርጾች*+ ሰረቀች። ዘዳግም 5:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ከእኔ በቀር* ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።+ ኢያሱ 23:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 እንዲሁም በመካከላችሁ ከቀሩት ከእነዚህ ብሔራት ጋር አትቀላቀሉ።+ ሌላው ቀርቶ የአማልክታቸውን ስም አታንሱ፤+ በእነሱም አትማሉ፤ ፈጽሞ አታገልግሏቸው እንዲሁም አትስገዱላቸው።+ 1 ቆሮንቶስ 10:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ከጣዖት አምልኮ ሽሹ።+
7 እንዲሁም በመካከላችሁ ከቀሩት ከእነዚህ ብሔራት ጋር አትቀላቀሉ።+ ሌላው ቀርቶ የአማልክታቸውን ስም አታንሱ፤+ በእነሱም አትማሉ፤ ፈጽሞ አታገልግሏቸው እንዲሁም አትስገዱላቸው።+