-
ዘፀአት 28:6-8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 “ከወርቅ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ ኤፉዱን ያዘጋጃሉ፤ ኤፉዱም ጥልፍ የተጠለፈበት ይሁን።+ 7 ኤፉዱ በሁለቱ የላይኛው ጫፎቹ ላይ እርስ በርስ የተያያዙ ሁለት የትከሻ ጥብጣቦች ይኖሩታል። 8 ኤፉዱ ወዲያ ወዲህ እንዳይንቀሳቀስ ለማሰር የሚያገለግለው ከኤፉዱ ጋር የተያያዘው በሽመና የተሠራው መቀነት+ ልክ እንደ ኤፉዱ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ የተሠራ መሆን ይኖርበታል።
-