የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 15:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 ማዕበሉም ከደናቸው፤ እነሱም እንደ ድንጋይ ወደ ጥልቁ ሰመጡ።+

  • ዘፀአት 15:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 አንተም እስትንፋስህን እፍ አልክ፤ ባሕሩም ከደናቸው፤+

      እነሱም ኃያል በሆኑ ውኃዎች ውስጥ እንደ አረር ሰመጡ።

  • ዘዳግም 11:3, 4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 እነሱ በግብፅ ይኸውም በግብፁ ንጉሥ በፈርዖን ፊትና በመላው ምድሩ ላይ ያሳየውን ተአምራዊ ምልክትም ሆነ ያደረገውን ነገር አልተመለከቱም፤+ 4 ወይም እናንተን እያሳደዱ ሳሉ በቀይ ባሕር ውስጥ በሰጠሙት በግብፅ ሠራዊት፣ በፈርዖን ፈረሶችና የጦር ሠረገሎች ላይ ያደረገውን አላዩም፤ ይሖዋም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ* አጠፋቸው።+

  • ኢያሱ 24:6, 7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 6 አባቶቻችሁን ከግብፅ ባወጣኋቸውና+ ወደ ባሕሩ በደረሳችሁ ጊዜ ግብፃውያኑ የጦር ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን አሰልፈው አባቶቻችሁን እየተከታተሉ እስከ ቀይ ባሕር ድረስ መጡ።+ 7 እነሱም ወደ ይሖዋ መጮኽ ጀመሩ፤+ በመሆኑም በእናንተና በግብፃውያን መካከል ጨለማ እንዲኖር አደረገ፤ ባሕሩንም በላያቸው ላይ በመመለስ አሰመጣቸው፤+ በግብፅ ያደረግኩትንም የገዛ ዓይኖቻችሁ አይተዋል።+ ከዚያም በምድረ በዳ ለብዙ ዓመታት* ኖራችሁ።+

  • ነህምያ 9:10, 11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 ከዚያም በፈርዖን፣ በአገልጋዮቹ ሁሉና በምድሩ በሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ፊት ምልክቶችንና ተአምራትን አሳየህ፤+ ይህን ያደረግከው በእነሱ ላይ የእብሪት ድርጊት+ እንደፈጸሙ ስላወቅክ ነው። ለራስህም እስከ ዛሬ ጸንቶ የኖረ ስም አተረፍክ።+ 11 በባሕሩ መሃል በደረቅ ምድር እንዲሻገሩ ባሕሩን በፊታቸው ከፈልክ፤+ አሳዳጆቻቸውንም የሚናወጥ ባሕር ውስጥ እንደተጣለ ድንጋይ ወደ ጥልቁ ወረወርካቸው።+

  • መዝሙር 78:53
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 53  በአስተማማኝ ሁኔታ መራቸው፤

      አንዳች ፍርሃትም አልተሰማቸውም፤+

      ባሕሩም ጠላቶቻቸውን ዋጠ።+

  • ዕብራውያን 11:29
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 29 እስራኤላውያን በደረቅ ምድር የሚሄዱ ያህል ቀይ ባሕርን በእምነት ተሻገሩ፤+ ይሁንና ግብፃውያን እንዲህ ለማድረግ በሞከሩ ጊዜ ሰመጡ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ