ዘፀአት 23:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 “ጉቦ አትቀበል፤ ምክንያቱም ጉቦ አጥርተው የሚያዩ ሰዎችን ዓይን ያሳውራል፤ እንዲሁም የጻድቅ ሰዎችን ቃል ሊያዛባ ይችላል።+ 1 ጢሞቴዎስ 3:2, 3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ስለዚህ የበላይ ተመልካች የማይነቀፍ፣ የአንዲት ሚስት ባል፣ በልማዶቹ ልከኛ የሆነ፣ ጤናማ አስተሳሰብ ያለው፣*+ ሥርዓታማ፣ እንግዳ ተቀባይ፣+ የማስተማር ብቃት ያለው፣+ 3 የማይሰክር፣*+ ኃይለኛ ያልሆነ፣* ይልቁንም ምክንያታዊ የሆነ፣+ የማይጣላ፣+ ገንዘብ ወዳድ ያልሆነ፣+ ቲቶ 1:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ምክንያቱም የበላይ ተመልካች በአምላክ የተሾመ መጋቢ እንደመሆኑ መጠን ከክስ ነፃ መሆን አለበት፤ በራሱ ሐሳብ የሚመራ፣+ ግልፍተኛ፣+ ሰካራም፣ ኃይለኛና* አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የሚስገበገብ ሊሆን አይገባም፤ 1 ጴጥሮስ 5:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 የበላይ ተመልካቾች ሆናችሁ በማገልገል* በአደራ የተሰጣችሁን የአምላክን መንጋ እንደ እረኞች ሆናችሁ ተንከባከቡ፤+ ሥራችሁን በግዴታ ሳይሆን በአምላክ ፊት በፈቃደኝነት ተወጡ፤+ አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በመመኘት ሳይሆን+ ለማገልገል በመጓጓት፣
2 ስለዚህ የበላይ ተመልካች የማይነቀፍ፣ የአንዲት ሚስት ባል፣ በልማዶቹ ልከኛ የሆነ፣ ጤናማ አስተሳሰብ ያለው፣*+ ሥርዓታማ፣ እንግዳ ተቀባይ፣+ የማስተማር ብቃት ያለው፣+ 3 የማይሰክር፣*+ ኃይለኛ ያልሆነ፣* ይልቁንም ምክንያታዊ የሆነ፣+ የማይጣላ፣+ ገንዘብ ወዳድ ያልሆነ፣+
7 ምክንያቱም የበላይ ተመልካች በአምላክ የተሾመ መጋቢ እንደመሆኑ መጠን ከክስ ነፃ መሆን አለበት፤ በራሱ ሐሳብ የሚመራ፣+ ግልፍተኛ፣+ ሰካራም፣ ኃይለኛና* አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የሚስገበገብ ሊሆን አይገባም፤
2 የበላይ ተመልካቾች ሆናችሁ በማገልገል* በአደራ የተሰጣችሁን የአምላክን መንጋ እንደ እረኞች ሆናችሁ ተንከባከቡ፤+ ሥራችሁን በግዴታ ሳይሆን በአምላክ ፊት በፈቃደኝነት ተወጡ፤+ አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በመመኘት ሳይሆን+ ለማገልገል በመጓጓት፣