13 ኢያሱ በኢያሪኮ አቅራቢያ ሳለ፣ ቀና ብሎ ሲመለከት የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ+ አንድ ሰው ፊት ለፊቱ ቆሞ አየ።+ ኢያሱም ወደ እሱ ሄዶ “ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን?” ሲል ጠየቀው። 14 እሱም መልሶ እንዲህ አለው፦ “አይደለሁም፤ እኔ አሁን የመጣሁት የይሖዋ ሠራዊት አለቃ ሆኜ ነው።”+ በዚህ ጊዜ ኢያሱ በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ በመስገድ “ታዲያ ጌታዬ ለአገልጋዩ የሚነግረው ምንድን ነው?” አለው።