ዘሌዋውያን 24:5, 6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 “አንተም የላመ ዱቄት ወስደህ የቀለበት ቅርጽ ያላቸው 12 ዳቦዎችን ጋግር። እያንዳንዱ ዳቦ ከሁለት አሥረኛ ኢፍ* ዱቄት የተዘጋጀ መሆን ይኖርበታል። 6 እነዚህንም በይሖዋ ፊት ባለው ከንጹሕ ወርቅ በተሠራው ጠረጴዛ+ ላይ ስድስት ስድስት አድርገህ በማነባበር በሁለት ረድፍ ታስቀምጣቸዋለህ።+ 1 ሳሙኤል 21:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በመሆኑም ካህኑ የተቀደሰውን ኅብስት ሰጠው፤+ ምክንያቱም ትኩስ ኅብስት በሚተካበት ቀን ከይሖዋ ፊት ከተነሳው ገጸ ኅብስት በስተቀር ሌላ ዳቦ አልነበረም። 1 ዜና መዋዕል 9:32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 ወንድሞቻቸው ከሆኑት ከቀዓታውያን አንዳንዶቹ የሚነባበረውን ዳቦ*+ በየሰንበቱ የማዘጋጀት+ ኃላፊነት ነበራቸው። 2 ዜና መዋዕል 13:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 በየጠዋቱና በየማታው+ ለይሖዋ የሚቃጠል መባ እንዲሁም ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን+ ያቀርባሉ፤ የሚነባበረውም ዳቦ*+ ከንጹሕ ወርቅ በተሠራው ጠረጴዛ ላይ ይቀመጣል፤ የወርቁን መቅረዝና+ መብራቶቹን በየማታው ያበራሉ፤+ ምክንያቱም እኛ በአምላካችን በይሖዋ ፊት ያለብንን ኃላፊነት እየተወጣን ነው፤ እናንተ ግን እሱን ትታችሁታል። ማቴዎስ 12:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ወደ አምላክ ቤት ገብቶ ከካህናት በስተቀር+ እሱም ሆነ ከእሱ ጋር የነበሩት ሰዎች እንዲበሉ ያልተፈቀደውን በአምላክ ፊት የቀረበ ኅብስት+ አልበሉም?
5 “አንተም የላመ ዱቄት ወስደህ የቀለበት ቅርጽ ያላቸው 12 ዳቦዎችን ጋግር። እያንዳንዱ ዳቦ ከሁለት አሥረኛ ኢፍ* ዱቄት የተዘጋጀ መሆን ይኖርበታል። 6 እነዚህንም በይሖዋ ፊት ባለው ከንጹሕ ወርቅ በተሠራው ጠረጴዛ+ ላይ ስድስት ስድስት አድርገህ በማነባበር በሁለት ረድፍ ታስቀምጣቸዋለህ።+
11 በየጠዋቱና በየማታው+ ለይሖዋ የሚቃጠል መባ እንዲሁም ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን+ ያቀርባሉ፤ የሚነባበረውም ዳቦ*+ ከንጹሕ ወርቅ በተሠራው ጠረጴዛ ላይ ይቀመጣል፤ የወርቁን መቅረዝና+ መብራቶቹን በየማታው ያበራሉ፤+ ምክንያቱም እኛ በአምላካችን በይሖዋ ፊት ያለብንን ኃላፊነት እየተወጣን ነው፤ እናንተ ግን እሱን ትታችሁታል።