-
ዘኁልቁ 4:14, 15አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 እንዲሁም በመሠዊያው ላይ ለማገልገል የሚጠቀሙባቸውን ዕቃዎች በሙሉ ይኸውም መኮስተሪያዎቹን፣ ሹካዎቹን፣ አካፋዎቹን፣ ጎድጓዳ ሳህኖቹንና የመሠዊያውን ዕቃዎች በሙሉ በላዩ ላይ ያደርጉበታል፤+ ከአቆስጣ ቆዳ የተሠራ መሸፈኛም ይደርቡበታል፤ ለመሸከሚያ የሚያገለግሉትንም መሎጊያዎች+ በቦታቸው ላይ ያደርጓቸዋል።
15 “አሮንና ወንዶች ልጆቹ ሰፈሩ ከመነሳቱ በፊት በቅዱሱ ስፍራ ያሉትን ነገሮችና የቅዱሱን ስፍራ ዕቃዎች በሙሉ ሸፍነው መጨረስ አለባቸው።+ ከዚያም የቀአት ወንዶች ልጆች ለመሸከም ይመጣሉ፤+ ሆኖም በቅዱሱ ስፍራ ያሉትን ነገሮች መንካት የለባቸውም፤ ከነኩ ግን ይሞታሉ።+ ከመገናኛ ድንኳኑ ጋር በተያያዘ እነዚህን ነገሮች የማከናወኑ ኃላፊነት* የተጣለው በቀአት ወንዶች ልጆች ላይ ነው።
-