-
ዘሌዋውያን 8:14-17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 ከዚያም ለኃጢአት መባ የሚሆነውን በሬ አመጣ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም እጆቻቸውን ለኃጢአት መባ በሚሆነው በሬ ራስ ላይ ጫኑ።+ 15 ሙሴም በሬውን አረደው፤ ደሙንም+ በጣቱ ወስዶ በሁሉም የመሠዊያው ጎኖች ላይ ያሉትን ቀንዶች ቀባ፤ መሠዊያውንም ከኃጢአት አነጻው፤ የቀረውንም ደም መሠዊያው ማስተሰረያ ይቀርብበት ዘንድ መሠዊያውን ለመቀደስ በሥሩ አፈሰሰው። 16 ከዚያም ሙሴ አንጀቱን የሸፈነውን ስብ ሁሉ፣ በጉበቱ ላይ ያለውን ሞራ፣ ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ያለውን ስብ ወስዶ በመሠዊያው ላይ እንዲጨሱ አደረገ።+ 17 ሙሴም ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ከበሬው የቀረውን፣ ቆዳውን፣ ሥጋውንና ፈርሱን ከሰፈሩ ውጭ በእሳት አቃጠለው።+
-