4 አንደኛውን ተባዕት የበግ ጠቦት ጠዋት ላይ፣ ሌላኛውን ተባዕት የበግ ጠቦት ደግሞ አመሻሹ ላይ አቅርቡ፤+ 5 ከእነዚህም ጋር ተጨቅጭቆ በተጠለለ አንድ አራተኛ ሂን ዘይት የተለወሰ አንድ አሥረኛ ኢፍ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ አቅርቡ።+ 6 ይህም በሲና ተራራ ላይ በወጣው ደንብ መሠረት ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው ዘወትር የሚቀርብ የሚቃጠል መባ+ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነው፤