ዘፀአት 6:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ሁሉን ቻይ አምላክ+ ሆኜ እገለጥላቸው ነበር፤ ይሖዋ የሚለውን ስሜን+ በተመለከተ ግን ራሴን ሙሉ በሙሉ አልገለጥኩላቸውም።+ ዘፀአት 33:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ሆኖም እሱ እንዲህ አለው፦ “እኔ ራሴ ጥሩነቴ ሁሉ በፊትህ እንዲያልፍ አደርጋለሁ፤ ይሖዋ የተባለውንም ስሜን በፊትህ አውጃለሁ።+ ሞገስ ላሳየው የምፈልገውን ሞገስ አሳየዋለሁ፤ ልምረው የምፈልገውን ደግሞ እምረዋለሁ።”+
19 ሆኖም እሱ እንዲህ አለው፦ “እኔ ራሴ ጥሩነቴ ሁሉ በፊትህ እንዲያልፍ አደርጋለሁ፤ ይሖዋ የተባለውንም ስሜን በፊትህ አውጃለሁ።+ ሞገስ ላሳየው የምፈልገውን ሞገስ አሳየዋለሁ፤ ልምረው የምፈልገውን ደግሞ እምረዋለሁ።”+