የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 22:27
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 27 ምክንያቱም የሚለብሰው ልብስ ይኸውም ሰውነቱ ላይ የሚጥለው ልብስ እሱ ብቻ ነው፤ አለዚያ ምን ለብሶ ይተኛል?+ እሱም ወደ እኔ በሚጮኽበት ጊዜ በእርግጥ እሰማዋለሁ፤ ምክንያቱም እኔ ሩኅሩኅ* ነኝ።+

  • 2 ዜና መዋዕል 30:9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 ወደ ይሖዋ ስትመለሱ ወንድሞቻችሁና ልጆቻችሁ በማረኳቸው ዘንድ ምሕረት ያገኛሉ፤+ ወደዚህች ምድር እንዲመለሱም ይለቋቸዋል፤+ አምላካችሁ ይሖዋ ሩኅሩኅና* መሐሪ ነውና፤+ ወደ እሱም ከተመለሳችሁ ፊቱን አያዞርባችሁም።”+

  • ነህምያ 9:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 ለመስማትም አሻፈረኝ አሉ፤+ በመካከላቸው የፈጸምካቸውን እጅግ አስደናቂ የሆኑ ነገሮች ረሱ፤ ከዚህ ይልቅ ግትሮች ሆኑ፤* በግብፅ ወደነበሩበት የባርነት ሕይወት ለመመለስም መሪ ሾሙ።+ አንተ ግን ይቅር ለማለት ዝግጁ የሆንክ፣* ሩኅሩኅ፣* መሐሪ፣ ለቁጣ የዘገየህና ታማኝ ፍቅርህ የበዛ* አምላክ ነህ፤+ እነሱንም አልተውካቸውም።+

  • መዝሙር 86:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን መሐሪና ሩኅሩኅ፣*

      ለቁጣ የዘገየህ እንዲሁም ታማኝ ፍቅርህና ታማኝነትህ* የበዛ አምላክ ነህ።+

  • ኢዩኤል 2:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤+

      ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋም ተመለሱ፤

      እሱ ሩኅሩኅና* መሐሪ፣ ለቁጣ የዘገየና+ ታማኝ ፍቅሩ የበዛ ነውና፤+

      ሊያመጣ ያሰበውንም ጥፋት መለስ ብሎ ያጤናል።*

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ