የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 7:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 ምክንያቱም ልጆችህ ሌሎች አማልክትን ያገለግሉ ዘንድ እኔን ከመከተል ዞር እንዲሉ ያደርጓቸዋል፤+ ከዚያም የይሖዋ ቁጣ በእናንተ ላይ ይነድዳል፤ አንተንም ወዲያው ያጠፋሃል።+

  • ዘዳግም 31:16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ አንተ መሞትህ ነው፤* ይህም ሕዝብ በሚሄድበት ምድር በዙሪያው ካሉ ባዕዳን አማልክት ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ይፈጽማል።+ እኔንም ይተዉኛል፤+ ከእነሱም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳሉ።+

  • መሳፍንት 2:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 እነሱ ግን መሳፍንቱን እንኳ ለመስማት ፈቃደኞች አልሆኑም፤ እንዲያውም ከሌሎች አማልክት ጋር አመነዘሩ፤ ለእነሱም ሰገዱ። የይሖዋን ትእዛዛት ያከብሩ የነበሩ አባቶቻቸው ከሄዱበት መንገድ ፈጥነው ዞር አሉ።+ እነሱ እንዳደረጉት ማድረግ ሳይችሉ ቀሩ።

  • መሳፍንት 8:33
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 33 እስራኤላውያን ጌድዮን ከሞተ ብዙም ሳይቆይ እንደገና ከባአል ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ፈጸሙ፤+ ባአልበሪትንም አምላካቸው አደረጉት።+

  • 1 ነገሥት 11:2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 2 እነሱም ይሖዋ ለእስራኤላውያን “ከእነሱ ጋር አትቀላቀሉ፤* እነሱም ከእናንተ ጋር አይቀላቀሉ፤ አለዚያ ያለምንም ጥርጥር ልባችሁ አማልክታቸውን ወደ መከተል እንዲያዘነብል ያደርጉታል”+ ብሎ ከነገራቸው ብሔራት ወገን ነበሩ። ሆኖም ሰለሞን ከእነሱ ጋር ተጣበቀ፤ ደግሞም አፈቀራቸው።

  • ነህምያ 13:26
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 26 የእስራኤል ንጉሥ ሰለሞን ኃጢአት የሠራው በእነሱ ምክንያት አይደለም? በብዙ ብሔራት መካከል እንደ እሱ ያለ ንጉሥ አልነበረም፤+ ደግሞም በአምላኩ ዘንድ የተወደደ+ ስለነበር አምላክ በመላው እስራኤል ላይ ንጉሥ አደረገው። ይሁንና ባዕዳን ሚስቶች እሱን እንኳ ኃጢአት እንዲሠራ አደረጉት።+

  • መዝሙር 106:28
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 28 ከዚያም በፌጎር የነበረውን ባአል አመለኩ፤*+

      ለሙታን የቀረቡትን መሥዋዕቶችም* በሉ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ