ዘፀአት 24:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 በመሆኑም ሙሴ ደሙን ወስዶ በሕዝቡ ላይ ረጨው፤+ እንዲህም አለ፦ “በእነዚህ ቃላት መሠረት ይሖዋ ከእናንተ ጋር የገባው ቃል ኪዳን ደም ይህ ነው።”+ ዘዳግም 4:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 እሱም እንድትጠብቁት ያዘዛችሁን ቃል ኪዳኑን ይኸውም አሥርቱን ትእዛዛት* ገለጸላችሁ።+ ከዚያም በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፋቸው።+