7 ሌዋውያን የሆኑት የሹዋ፣ ባኒ፣ ሸረበያህ፣+ ያሚን፣ አቁብ፣ ሻበታይ፣ ሆዲያህ፣ ማአሴያህ፣ ቀሊጣ፣ አዛርያስ፣ ዮዛባድ፣+ ሃናን እና ፐላያህ ደግሞ ሕዝቡ እዚያው ቆሞ ሳለ ሕጉን ለሕዝቡ ያብራሩ ነበር።+ 8 እነሱም ከመጽሐፉ ይኸውም ከእውነተኛው አምላክ ሕግ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በማንበብ ሕጉን በግልጽ ያብራሩና ትርጉሙ ምን እንደሆነ ይናገሩ ነበር፤ በዚህ መንገድ የተነበበውን ነገር ማስተዋል እንዲችል ሕዝቡን ይረዱት ነበር።+