10 “‘ከእስራኤል ቤት የሆነ ማንኛውም ሰው ወይም በመካከላችሁ የሚኖር የትኛውም የባዕድ አገር ሰው ምንም ዓይነት ደም ቢበላ፣+ ደም በሚበላው ሰው ላይ በእርግጥ ፊቴን አጠቁርበታለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። 11 ምክንያቱም የሥጋ ሕይወት ያለው በደሙ ውስጥ ነው፤+ ለራሳችሁም ማስተሰረያ እንዲሆን እኔ ራሴ ደሙን ለእናንተ ስል ለመሠዊያው ሰጥቼዋለሁ፤+ ምክንያቱም በውስጡ ባለው ሕይወት አማካኝነት የሚያስተሰርየው ደሙ ነው።+