ዘፀአት 28:36 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 36 “ከንጹሕ ወርቅም የሚያብረቀርቅ ጠፍጣፋ ወርቅ ሠርተህ ልክ ማኅተም በሚቀረጽበት መንገድ ‘ቅድስና የይሖዋ ነው’+ ብለህ ትቀርጽበታለህ። ዘሌዋውያን 11:45 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 45 አምላካችሁ መሆኔን ለማስመሥከር ከግብፅ ምድር መርቼ ያወጣኋችሁ እኔ ይሖዋ ነኝና፤+ እኔ ቅዱስ ስለሆንኩ+ እናንተም ቅዱሳን መሆን አለባችሁ።+ ዘሌዋውያን 20:7, 8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 “‘እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ስለሆንኩ ራሳችሁን ቀድሱ፤ ቅዱሳንም ሁኑ።+ 8 ደንቦቼን ጠብቁ፤ እንዲሁም ፈጽሟቸው።+ የምቀድሳችሁ እኔ ይሖዋ ነኝ።+