13 “‘እንግዲህ ፈሳሹ ቢቆምና ሰውየው ከፈሳሹ ቢነጻ ንጹሕ ለመሆን ሰባት ቀን ይቁጠር፤ ልብሶቹን ይጠብ፤ ገላውንም በምንጭ ውኃ ይታጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል።+ 14 በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶችን ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶችን ይውሰድ፤+ እነዚህንም ይዞ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በይሖዋ ፊት በመቅረብ ለካህኑ ይስጥ። 15 ካህኑም አንዱን የኃጢአት መባ ሌላኛውን ደግሞ የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርባቸዋል፤ ካህኑም ስለ ፈሳሹ ለሰውየው በይሖዋ ፊት ያስተሰርይለታል።