ዘዳግም 23:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 “ለአምላክህ ለይሖዋ ስእለት ከተሳልክ+ ለመፈጸም አትዘግይ።+ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ በእርግጥ ከአንተ ይፈልገዋል፤ አለዚያ ኃጢአት ይሆንብሃል።+ መዝሙር 116:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 በሕዝቡ ሁሉ ፊትስእለቴን ለይሖዋ እፈጽማለሁ።+ መዝሙር 119:106 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 106 የጽድቅ ፍርዶችህን ለመጠበቅ ምያለሁ፤ደግሞም እፈጽመዋለሁ። መክብብ 5:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ለአምላክ ስእለት በምትሳልበት ጊዜ ሁሉ ስእለትህን ለመፈጸም አትዘግይ፤+ እሱ በሞኞች አይደሰትምና።+ ስእለትህን ፈጽም።+ ማቴዎስ 5:33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 “ከዚህም ሌላ በጥንት ዘመን ለነበሩት ‘በከንቱ አትማል፤+ ይልቁንም ለይሖዋ* የተሳልከውን ፈጽም’+ እንደተባለ ሰምታችኋል።