ዘፀአት 26:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 “ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግ እንዲሁም በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ የበፍታ ድር መጋረጃ+ ትሠራለህ። በላዩም ላይ ኪሩቦች ይጠለፉበታል። ዘፀአት 40:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 የምሥክሩን ታቦት በውስጡ ካስቀመጥክ+ በኋላ ታቦቱን በመጋረጃው ከልለው።+ ዘሌዋውያን 16:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ይሖዋም እንዲህ አለው፦ “እኔ ከመክደኛው በላይ+ በደመና ውስጥ+ ስለምገለጥ በመጋረጃው ውስጥ+ ወዳለው ቅዱስ ስፍራ+ ይኸውም በታቦቱ ላይ ወዳለው መክደኛ ፊት በፈለገው ጊዜ እንዳይገባና በዚህም የተነሳ እንዳይሞት+ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው።
2 ይሖዋም እንዲህ አለው፦ “እኔ ከመክደኛው በላይ+ በደመና ውስጥ+ ስለምገለጥ በመጋረጃው ውስጥ+ ወዳለው ቅዱስ ስፍራ+ ይኸውም በታቦቱ ላይ ወዳለው መክደኛ ፊት በፈለገው ጊዜ እንዳይገባና በዚህም የተነሳ እንዳይሞት+ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው።