ዘዳግም 31:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ደፋርና ብርቱ ሁኑ።+ ከእናንተ ጋር የሚሄደው አምላካችሁ ይሖዋ ስለሆነ አትፍሯቸው ወይም በፊታቸው አትሸበሩ።+ እሱ አይጥላችሁም ወይም አይተዋችሁም።”+ ኢያሱ 1:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ይህን ሕዝብ ለአባቶቻቸው ልሰጣቸው ወደማልኩላቸው ምድር+ የምታስገባው አንተ ስለሆንክ ደፋርና ብርቱ ሁን።+ ኢያሱ 1:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ደፋርና ብርቱ ሁን ብዬ አዝዤህ አልነበረም? አምላክህ ይሖዋ በምትሄድበት ሁሉ ከአንተ ጋር ስለሆነ አትሸበር፤ አትፍራ።”+