ዘፍጥረት 12:1-3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ይሖዋም አብራምን እንዲህ አለው፦ “ከአገርህ፣ ከዘመዶችህና ከአባትህ ቤት ወጥተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ።+ 2 አንተን ታላቅ ብሔር አደርግሃለሁ፤ እንዲሁም እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ታላቅ አደርገዋለሁ፤ አንተም በረከት ትሆናለህ።+ 3 የሚባርኩህን እባርካለሁ፤ የሚረግምህንም እረግማለሁ፤+ የምድር ሕዝቦችም ሁሉ በአንተ አማካኝነት ይባረካሉ።”*+ ዘፍጥረት 27:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 ሕዝቦች ያገልግሉህ፤ ብሔራትም ይስገዱልህ። የወንድሞችህ ጌታ ሁን፤ የእናትህም ወንዶች ልጆች ይስገዱልህ።+ የሚረግሙህ ሁሉ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚባርኩህም ሁሉ የተባረኩ ይሁኑ።”+
12 ይሖዋም አብራምን እንዲህ አለው፦ “ከአገርህ፣ ከዘመዶችህና ከአባትህ ቤት ወጥተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ።+ 2 አንተን ታላቅ ብሔር አደርግሃለሁ፤ እንዲሁም እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ታላቅ አደርገዋለሁ፤ አንተም በረከት ትሆናለህ።+ 3 የሚባርኩህን እባርካለሁ፤ የሚረግምህንም እረግማለሁ፤+ የምድር ሕዝቦችም ሁሉ በአንተ አማካኝነት ይባረካሉ።”*+
29 ሕዝቦች ያገልግሉህ፤ ብሔራትም ይስገዱልህ። የወንድሞችህ ጌታ ሁን፤ የእናትህም ወንዶች ልጆች ይስገዱልህ።+ የሚረግሙህ ሁሉ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚባርኩህም ሁሉ የተባረኩ ይሁኑ።”+