ዘኁልቁ 27:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 በመሆኑም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “መንፈስ ያለበትን የነዌን ልጅ ኢያሱን ወስደህ እጅህን ጫንበት።+ ዘዳግም 3:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 በዚህ ሕዝብ ፊት የሚሻገረውም+ ሆነ አንተ ያየሃትን ምድር እንዲወርሱ የሚያደርገው ኢያሱ ስለሆነ እሱን መሪ አድርገህ ሹመው፤+ አደፋፍረው፤ አበረታታውም።’ ኢያሱ 1:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 “አገልጋዬ ሙሴ ሞቷል።+ እንግዲህ አንተም ሆንክ ይህ ሕዝብ ተነስታችሁ ዮርዳኖስን በመሻገር ለእስራኤላውያን ወደምሰጣቸው ምድር ግቡ።+