5 የእስራኤል የበኩር ልጅ የሆነው የሮቤል+ ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። እሱ በኩር ቢሆንም እንኳ የአባቱን መኝታ ስላረከሰ+ የብኩርና መብቱ ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ+ ወንዶች ልጆች ተሰጠ፤ ከዚህም የተነሳ በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ የብኩርና መብት እንዳለው ተደርጎ አልተመዘገበም። 2 ይሁዳ+ ከወንድሞቹ የሚበልጥ ከመሆኑም ሌላ መሪ+ የሚሆነው የተገኘው ከእሱ ነው፤ ሆኖም የብኩርና መብቱን ያገኘው ዮሴፍ ነበር።