ዘፀአት 15:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ይሖዋ ሆይ፣ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው?+ በቅድስናው ኃያል መሆኑን የሚያሳይ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?+ በመዝሙር ልትወደስ የሚገባህ የምትፈራ አምላክ ነህ፤ ድንቅ ነገሮችን ታደርጋለህ።+ 2 ሳሙኤል 7:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ በእርግጥም ታላቅ+ የሆንከው ለዚህ ነው። እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤+ ከአንተ በቀር አምላክ የለም፤+ በጆሯችን የሰማነው ነገር ሁሉ ይህን ያረጋግጣል። 1 ነገሥት 8:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 እንዲህም አለ፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ በፊቱ በሙሉ ልባቸው ለሚመላለሱ+ አገልጋዮቹ ቃል ኪዳኑን የሚጠብቅና ታማኝ ፍቅር+ የሚያሳይ እንደ አንተ ያለ አምላክ በላይ በሰማይም ሆነ በታች በምድር የለም።+ መዝሙር 86:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ይሖዋ ሆይ፣ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ የለም፤+ከአንተ ሥራ ጋር የሚወዳደር አንድም ሥራ የለም።+ ኤርምያስ 10:6, 7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ይሖዋ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም።+ አንተ ታላቅ ነህ፤ ስምህም ታላቅና ኃያል ነው። 7 የብሔራት ንጉሥ ሆይ፣+ አንተን የማይፈራ ማን ነው? አንተ ልትፈራ ይገባሃልና፤ምክንያቱም ከብሔራት ጠቢባን ሁሉ እንዲሁም ከመንግሥቶቻቸው ሁሉ መካከልእንደ አንተ ያለ ማንም የለም።+
11 ይሖዋ ሆይ፣ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው?+ በቅድስናው ኃያል መሆኑን የሚያሳይ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?+ በመዝሙር ልትወደስ የሚገባህ የምትፈራ አምላክ ነህ፤ ድንቅ ነገሮችን ታደርጋለህ።+
22 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ በእርግጥም ታላቅ+ የሆንከው ለዚህ ነው። እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤+ ከአንተ በቀር አምላክ የለም፤+ በጆሯችን የሰማነው ነገር ሁሉ ይህን ያረጋግጣል።
23 እንዲህም አለ፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ በፊቱ በሙሉ ልባቸው ለሚመላለሱ+ አገልጋዮቹ ቃል ኪዳኑን የሚጠብቅና ታማኝ ፍቅር+ የሚያሳይ እንደ አንተ ያለ አምላክ በላይ በሰማይም ሆነ በታች በምድር የለም።+
6 ይሖዋ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም።+ አንተ ታላቅ ነህ፤ ስምህም ታላቅና ኃያል ነው። 7 የብሔራት ንጉሥ ሆይ፣+ አንተን የማይፈራ ማን ነው? አንተ ልትፈራ ይገባሃልና፤ምክንያቱም ከብሔራት ጠቢባን ሁሉ እንዲሁም ከመንግሥቶቻቸው ሁሉ መካከልእንደ አንተ ያለ ማንም የለም።+