ዘፀአት 23:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 “ጉቦ አትቀበል፤ ምክንያቱም ጉቦ አጥርተው የሚያዩ ሰዎችን ዓይን ያሳውራል፤ እንዲሁም የጻድቅ ሰዎችን ቃል ሊያዛባ ይችላል።+ ዘዳግም 16:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 “አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ከተሞች ሁሉ ለእያንዳንዱ ነገድ ዳኞችንና አለቆችን ሹም፤+ እነሱም ለሕዝቡ የጽድቅ ፍርድ ይፍረዱ። ዮሐንስ 7:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 የሰውን ውጫዊ ገጽታ በማየት አትፍረዱ፤* ከዚህ ይልቅ በጽድቅ ፍረዱ።”+