የሐዋርያት ሥራ 20:35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 እናንተም እንዲሁ እየሠራችሁ ደካማ የሆኑትን መርዳት እንዳለባችሁ በሁሉም ነገር አሳይቻችኋለሁ፤+ እንዲሁም ‘ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል’+ በማለት ጌታ ኢየሱስ ራሱ የተናገረውን ቃል ማስታወስ ይኖርባችኋል።” 2 ቆሮንቶስ 9:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 አምላክ በደስታ የሚሰጠውን ሰው ስለሚወድ+ እያንዳንዱ ሰው ቅር እያለው* ወይም ተገዶ ሳይሆን በልቡ ያሰበውን ይስጥ።+ 1 ጢሞቴዎስ 6:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 በተጨማሪም መልካም ነገር እንዲያደርጉ፣ በመልካም ሥራዎች ባለጸጋ እንዲሆኑ እንዲሁም ለጋሶችና ለሌሎች ለማካፈል ዝግጁ እንዲሆኑ ምከራቸው፤+ ዕብራውያን 13:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 በተጨማሪም መልካም ማድረግንና ያላችሁን ነገር ለሌሎች ማካፈልን አትርሱ፤+ አምላክ እንዲህ ባሉት መሥዋዕቶች እጅግ ይደሰታልና።+
35 እናንተም እንዲሁ እየሠራችሁ ደካማ የሆኑትን መርዳት እንዳለባችሁ በሁሉም ነገር አሳይቻችኋለሁ፤+ እንዲሁም ‘ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል’+ በማለት ጌታ ኢየሱስ ራሱ የተናገረውን ቃል ማስታወስ ይኖርባችኋል።”