ዘፀአት 13:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ከዚያም ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አለ፦ “ከግብፅ ከባርነት ቤት የወጣችሁበትን ይህን ቀን አስቡ፤+ ምክንያቱም ይሖዋ በኃያል ክንድ ከዚህ አውጥቷችኋል።+ በመሆኑም እርሾ የገባበት ምንም ነገር መበላት የለበትም። ዘሌዋውያን 23:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 “‘በዚህ ወር 15ኛ ቀን ላይ የቂጣ በዓል ለይሖዋ ይከበራል።+ ለሰባት ቀንም ቂጣ መብላት ይኖርባችኋል።+ ዘኁልቁ 28:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 በዚሁ ወር በ15ኛው ቀን በዓል ይሆናል። ለሰባት ቀን ቂጣ ይበላል።+ 1 ቆሮንቶስ 5:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ስለዚህ በዓሉን+ በአሮጌ እርሾ እንዲሁም በክፋትና በኃጢአት እርሾ ሳይሆን እርሾ በሌለበት በቅንነትና በእውነት ቂጣ እናክብር።
3 ከዚያም ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አለ፦ “ከግብፅ ከባርነት ቤት የወጣችሁበትን ይህን ቀን አስቡ፤+ ምክንያቱም ይሖዋ በኃያል ክንድ ከዚህ አውጥቷችኋል።+ በመሆኑም እርሾ የገባበት ምንም ነገር መበላት የለበትም።