14 ከዚያም ማኅበረሰቡ ሁሉ ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ፤ ሕዝቡም ሌሊቱን ሙሉ ሲጮኽና ሲያለቅስ አደረ።+ 2 እስራኤላውያንም በሙሉ በሙሴና በአሮን ላይ ያጉረመርሙ ጀመር፤+ መላው ማኅበረሰብ እንዲህ አላቸው፦ “ምነው በግብፅ ምድር ሳለን ሞተን ባረፍነው፤ ወይም ምናለ በዚህ ምድረ በዳ በሞትን! 3 ይሖዋ በሰይፍ እንድንሞት ወደዚህ ምድር ያመጣን ለምንድን ነው?+ እንግዲህ ሚስቶቻችንና ልጆቻችን ይማረካሉ።+ ታዲያ ወደ ግብፅ ብንመለስ አይሻለንም?”+