ዘሌዋውያን 22:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ላምን ከጥጃዋ ወይም በግን ከግልገሏ ጋር በአንድ ቀን አትረዱ።+ መዝሙር 145:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ይሖዋ ለሁሉም ጥሩ ነው፤+ምሕረቱም በሥራው ሁሉ ላይ ይታያል። ምሳሌ 12:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ጻድቅ የቤት እንስሳቱን* ይንከባከባል፤+ክፉዎች ግን ርኅራኄያቸው እንኳ ጭካኔ ነው። ማቴዎስ 10:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 ሁለት ድንቢጦች የሚሸጡት አነስተኛ ዋጋ ባላት ሳንቲም* አይደለም? ሆኖም ከእነሱ አንዷም እንኳ አባታችሁ ሳያውቅ መሬት ላይ አትወድቅም።+