ዘፍጥረት 4:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ከዚያ በኋላ ቃየን ወንድሙን አቤልን “ና ወደ ሜዳ እንሂድ” አለው። በሜዳው ላይ ሳሉም ቃየን ወንድሙን አቤልን ደብድቦ ገደለው።+ ዘኁልቁ 35:20, 21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 አንድ ሰው ሌላውን በጥላቻ ተገፋፍቶ ቢገፈትረው ወይም ተንኮል አስቦ* የሆነ ነገር ቢወረውርበትና ግለሰቡ ቢሞት+ 21 አሊያም በጥላቻ ተነሳስቶ በእጁ ቢመታውና ቢሞት መቺው ያለምንም ጥርጥር ይገደላል። እሱ ነፍሰ ገዳይ ነው። ደም ተበቃዩም ነፍሰ ገዳዩን ባገኘው ጊዜ ይገድለዋል። ያዕቆብ 2:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 “አታመንዝር”+ ያለው እሱ “አትግደል”+ የሚል ትእዛዝም ሰጥቷልና። እንግዲህ ምንዝር ባትፈጽምም እንኳ ከገደልክ ሕግ ተላላፊ ሆነሃል።
20 አንድ ሰው ሌላውን በጥላቻ ተገፋፍቶ ቢገፈትረው ወይም ተንኮል አስቦ* የሆነ ነገር ቢወረውርበትና ግለሰቡ ቢሞት+ 21 አሊያም በጥላቻ ተነሳስቶ በእጁ ቢመታውና ቢሞት መቺው ያለምንም ጥርጥር ይገደላል። እሱ ነፍሰ ገዳይ ነው። ደም ተበቃዩም ነፍሰ ገዳዩን ባገኘው ጊዜ ይገድለዋል።