መሳፍንት 11:35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 እሱም ባያት ጊዜ ልብሱን ቀደደ፤ እንዲህም አለ፦ “ወዮ፣ ልጄ! ልቤን ሰበርሽው፤* እንግዲህ ከቤት የማስወጣው አንቺን ነው። አንዴ ለይሖዋ ቃል ገብቻለሁ፤ ልመልሰውም አልችልም።”+ 1 ሳሙኤል 14:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ሆኖም ሳኦል “ጠላቶቼን ከመበቀሌ በፊት እስከ ማታ ድረስ እህል የሚቀምስ ሰው የተረገመ ይሁን!” በማለት ሕዝቡን አስምሎ ስለነበር በዚያ ዕለት የእስራኤል ሰዎች ተጨንቀው ዋሉ። በመሆኑም ከሕዝቡ መካከል አንድም ሰው እህል አልቀመሰም።+ ማቴዎስ 5:33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 “ከዚህም ሌላ በጥንት ዘመን ለነበሩት ‘በከንቱ አትማል፤+ ይልቁንም ለይሖዋ* የተሳልከውን ፈጽም’+ እንደተባለ ሰምታችኋል።
35 እሱም ባያት ጊዜ ልብሱን ቀደደ፤ እንዲህም አለ፦ “ወዮ፣ ልጄ! ልቤን ሰበርሽው፤* እንግዲህ ከቤት የማስወጣው አንቺን ነው። አንዴ ለይሖዋ ቃል ገብቻለሁ፤ ልመልሰውም አልችልም።”+
24 ሆኖም ሳኦል “ጠላቶቼን ከመበቀሌ በፊት እስከ ማታ ድረስ እህል የሚቀምስ ሰው የተረገመ ይሁን!” በማለት ሕዝቡን አስምሎ ስለነበር በዚያ ዕለት የእስራኤል ሰዎች ተጨንቀው ዋሉ። በመሆኑም ከሕዝቡ መካከል አንድም ሰው እህል አልቀመሰም።+