ዘዳግም 31:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ደፋርና ብርቱ ሁኑ።+ ከእናንተ ጋር የሚሄደው አምላካችሁ ይሖዋ ስለሆነ አትፍሯቸው ወይም በፊታቸው አትሸበሩ።+ እሱ አይጥላችሁም ወይም አይተዋችሁም።”+ ኢያሱ 1:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም።+ ከሙሴ ጋር እንደነበርኩ ሁሉ ከአንተም ጋር እሆናለሁ።+ አልጥልህም ወይም አልተውህም።+