-
ኢያሱ 22:1-4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 ከዚያም ኢያሱ ሮቤላውያንን፣ ጋዳውያንንና የምናሴን ነገድ እኩሌታ ጠርቶ 2 እንዲህ አላቸው፦ “የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ያዘዛችሁን ሁሉ ፈጽማችኋል፤+ እኔም ባዘዝኳችሁ ነገር ሁሉ ቃሌን ሰምታችኋል።+ 3 በእነዚህ ሁሉ ጊዜያት እስከ ዛሬ ድረስ ወንድሞቻችሁን አልተዋችሁም፤+ አምላካችሁ ይሖዋ ከሰጣችሁ ትእዛዝ ጋር በተያያዘ ግዴታችሁን ተወጥታችኋል።+ 4 እንግዲህ አሁን አምላካችሁ ይሖዋ ለወንድሞቻችሁ ቃል በገባላቸው መሠረት እረፍት ሰጥቷቸዋል።+ በመሆኑም የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ከዮርዳኖስ ማዶ* ርስት አድርጎ በሰጣችሁ ምድር ወደሚገኙት ድንኳኖቻችሁ መመለስ ትችላላችሁ።+
-