-
ዘዳግም 3:19, 20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
19 ሚስቶቻችሁ፣ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ብቻ (መቼም ብዙ ከብቶች እንዳሏችሁ አውቃለሁ) በሰጠኋችሁ ከተሞች ውስጥ ይቀራሉ፤ 20 ይህም ይሖዋ ልክ ለእናንተ እንዳደረገላችሁ ሁሉ ለወንድሞቻችሁም እረፍት እስኪሰጣቸው እንዲሁም አምላካችሁ ይሖዋ ከዮርዳኖስ ማዶ የሚሰጣቸውን ምድር ርስት አድርገው እስኪወርሱ ድረስ ነው። ከዚያ በኋላ እያንዳንዳችሁ ወደሰጠኋችሁ ወደየራሳችሁ ርስት ትመለሳላችሁ።’+
-
-
ዘዳግም 29:8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 ከዚያም ምድራቸውን ወስደን ለሮቤላውያን፣ ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገን ሰጠናቸው።+
-
-
ኢያሱ 13:8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 የተቀረው የምናሴ ነገድ እኩሌታና ሮቤላውያን እንዲሁም ጋዳውያን የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ በሰጣቸው መሠረት ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ርስታቸውን ወስደዋል፤+
-