የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 15:14-16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ሕዝቦችም ይሰማሉ፤+ ይንቀጠቀጣሉ፤

      የፍልስጤም ነዋሪዎችም ምጥ ይይዛቸዋል።

      15 በዚያን ጊዜ የኤዶም አለቆች ይሸበራሉ፤

      የሞዓብ ኃያላን ገዢዎች ብርክ ይይዛቸዋል።+

      የከነአን ነዋሪዎችም ሁሉ ልባቸው ይከዳቸዋል።+

      16 ፍርሃትና ድንጋጤ ይወድቅባቸዋል።+

      ይሖዋ ሆይ፣ ሕዝቦችህ አልፈው እስኪሄዱ ድረስ፣

      አንተ የፈጠርካቸው ሕዝቦች+ አልፈው እስኪሄዱ ድረስ፣+

      ከክንድህ ታላቅነት የተነሳ እንደ ድንጋይ ደርቀው ይቀራሉ።

  • ኢያሱ 2:9-11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 እንዲህም አለቻቸው፦ “ይሖዋ ምድሪቱን እንደሚሰጣችሁ አውቃለሁ፤+ እኛም እናንተን በመፍራት ተሸብረናል።+ የምድሪቱ ነዋሪዎች በሙሉ በእናንተ የተነሳ ልባቸው ከድቷቸዋል፤+ 10 ምክንያቱም ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ ይሖዋ ቀይ ባሕርን በፊታችሁ እንዴት እንዳደረቀው+ እንዲሁም ከዮርዳኖስ ማዶ* በደመሰሳችኋቸው በሁለቱ የአሞራውያን ነገሥታት፣ በሲሖንና+ በኦግ+ ላይ ምን እንዳደረጋችሁ ሰምተናል። 11 ይህን ስንሰማ ልባችን ቀለጠ፤ በእናንተም የተነሳ ወኔ ያልከዳው ማንም አልነበረም፤ ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ በላይ በሰማይ በታችም በምድር አምላክ ነው።+

  • ኢያሱ 5:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ* የሚገኙት የአሞራውያን+ ነገሥታት ሁሉ እንዲሁም በባሕሩ አጠገብ ያሉት የከነአናውያን+ ነገሥታት በሙሉ ይሖዋ እስራኤላውያን ዮርዳኖስን እስኪሻገሩ ድረስ የወንዙን ውኃ በፊታቸው እንዳደረቀው ሲሰሙ ልባቸው ቀለጠ፤+ በእስራኤላውያንም የተነሳ ወኔ ከድቷቸው ነበር።*+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ