1 ሳሙኤል 28:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ፍልስጤማውያንም ተሰብስበው በመምጣት በሹነም+ ሰፈሩ። ሳኦል ደግሞ እስራኤላውያንን በሙሉ አሰባሰበ፤ እነሱም በጊልቦአ+ ሰፈሩ። 1 ነገሥት 1:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ስለዚህ በመላው የእስራኤል ግዛት በመዘዋወር ቆንጆ ልጃገረድ ፈለጉ፤ ሹነማዊቷን+ አቢሻግንም+ አገኙ፤ ወደ ንጉሡም አመጧት። 2 ነገሥት 4:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 አንድ ቀን ኤልሳዕ ወደ ሹነም+ ሄደ፤ በዚያም አንዲት ታዋቂ ሴት ነበረች፤ እሷም ምግብ እንዲበላ አጥብቃ ለመነችው።+ እሱም በዚያ ባለፈ ቁጥር ምግብ ለመብላት ወደዚያ ጎራ ይል ነበር።
8 አንድ ቀን ኤልሳዕ ወደ ሹነም+ ሄደ፤ በዚያም አንዲት ታዋቂ ሴት ነበረች፤ እሷም ምግብ እንዲበላ አጥብቃ ለመነችው።+ እሱም በዚያ ባለፈ ቁጥር ምግብ ለመብላት ወደዚያ ጎራ ይል ነበር።