ዘፀአት 21:12, 13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 “አንድ ሰው ሌላውን ሰው መትቶ ቢገድል ገዳዩ ይገደል።+ 13 ሆኖም የገደለው ሆን ብሎ ባይሆንና እውነተኛው አምላክ ይህ ነገር እንዲሆን ቢፈቅድ ገዳዩ የሚሸሽበት ቦታ እኔ አዘጋጅልሃለሁ።+ ዘኁልቁ 35:14, 15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 የመማጸኛ ከተሞች ሆነው እንዲያገለግሉ ከዮርዳኖስ ወዲህ ሦስት ከተሞችን፣+ በከነአን ምድር ደግሞ ሦስት ከተሞችን+ ትሰጣላችሁ። 15 እነዚህ ስድስት ከተሞች ለእስራኤላውያንም ሆነ ለባዕድ አገር ሰው+ አሊያም በመካከላቸው ለሚኖር ሰፋሪ ሳያስበው ሰው የገደለ* ማንኛውም ሰው ሸሽቶ የሚጠጋባቸው ከተሞች ሆነው ያገለግላሉ።+ ዘዳግም 4:41 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 41 በዚያን ጊዜ ሙሴ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ሦስት ከተሞችን ለየ።+
12 “አንድ ሰው ሌላውን ሰው መትቶ ቢገድል ገዳዩ ይገደል።+ 13 ሆኖም የገደለው ሆን ብሎ ባይሆንና እውነተኛው አምላክ ይህ ነገር እንዲሆን ቢፈቅድ ገዳዩ የሚሸሽበት ቦታ እኔ አዘጋጅልሃለሁ።+
14 የመማጸኛ ከተሞች ሆነው እንዲያገለግሉ ከዮርዳኖስ ወዲህ ሦስት ከተሞችን፣+ በከነአን ምድር ደግሞ ሦስት ከተሞችን+ ትሰጣላችሁ። 15 እነዚህ ስድስት ከተሞች ለእስራኤላውያንም ሆነ ለባዕድ አገር ሰው+ አሊያም በመካከላቸው ለሚኖር ሰፋሪ ሳያስበው ሰው የገደለ* ማንኛውም ሰው ሸሽቶ የሚጠጋባቸው ከተሞች ሆነው ያገለግላሉ።+