2 “እስራኤላውያንን ከሚወርሱት ርስት ላይ ለሌዋውያኑ መኖሪያ የሚሆኑ ከተሞችን እንዲሰጧቸው እዘዛቸው፤+ በከተሞቹም ዙሪያ ያለውን የግጦሽ መሬት ለሌዋውያኑ መስጠት አለባቸው።+ 3 ከተሞቹ ለእነሱ መኖሪያ፣ የግጦሽ ቦታዎቹ ደግሞ ለከብቶቻቸውና ለዕቃዎቻቸው እንዲሁም ለሌሎች እንስሶቻቸው ይሆናሉ። 4 ለሌዋውያኑ የምትሰጧቸው የከተሞቹ የግጦሽ ቦታዎች ከከተማው ቅጥር በሁሉም አቅጣጫ 1,000 ክንድ ይሆናል።