-
ዘኁልቁ 32:25-29አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
25 የጋድ ልጆችና የሮቤል ልጆችም ሙሴን እንዲህ አሉት፦ “እኛ አገልጋዮችህ ጌታችን እንዳዘዘን እናደርጋለን። 26 ልጆቻችን፣ ሚስቶቻችን፣ ከብቶቻችንና እንስሶቻችን በሙሉ በጊልያድ ከተሞች ውስጥ ይቆያሉ፤+ 27 ሆኖም እኛ አገልጋዮችህ ይኸውም በይሖዋ ፊት ጦርነት ለመግጠም የታጠቅን እያንዳንዳችን ልክ ጌታችን በተናገረው መሠረት እንሻገራለን።”+
28 በመሆኑም ሙሴ ለካህኑ ለአልዓዛር፣ ለነዌ ልጅ ለኢያሱና ለእስራኤል ነገዶች የአባቶች ቤት መሪዎች እነሱን በተመለከተ ትእዛዝ ሰጠ። 29 ሙሴም እንዲህ አላቸው፦ “የጋድ ልጆችና የሮቤል ልጆች ይኸውም በይሖዋ ፊት ለጦርነት የታጠቀ እያንዳንዱ ሰው ከእናንተ ጋር ዮርዳኖስን ከተሻገረ፣ ምድሪቱም በፊታችሁ ከተገዛች የጊልያድን ምድር ርስት አድርጋችሁ ትሰጧቸዋላችሁ።+
-