ዘዳግም 13:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 እናንተ አምላካችሁን ይሖዋን ተከተሉ፤ እሱን ፍሩ፤ ትእዛዛቱን ጠብቁ፤ ቃሉን ስሙ፤ እሱን አገልግሉ፤ እንዲሁም እሱን አጥብቃችሁ ያዙ።+ 1 ዮሐንስ 5:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 አምላክን መውደድ ማለት ትእዛዛቱን መጠበቅ ማለት ነውና፤+ ትእዛዛቱ ደግሞ ከባድ አይደሉም፤+