-
ዘሌዋውያን 26:3-12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 “‘ባወጣኋቸው ደንቦች መሠረት ብትሄዱና ትእዛዛቴን ብትጠብቁ እንዲሁም ብትፈጽሙ+ 4 ዝናብን በወቅቱ አዘንብላችኋለሁ፤+ ምድሪቱም ምርቷን ትሰጣለች፤+ የሜዳ ዛፎችም ፍሬያቸውን ይሰጣሉ። 5 ገና እህላችሁን ወቅታችሁ ሳትጨርሱ ወይናችሁን የምትሰበስቡበት ጊዜ ይደርሳል፤ ገና ወይኑን ሰብስባችሁ ሳትጨርሱ ደግሞ ዘር የምትዘሩበት ጊዜ ይመጣል፤ ምግባችሁን እስክትጠግቡ ድረስ ትበላላችሁ፤ በምድራችሁም ያለስጋት ትቀመጣላችሁ።+ 6 በምድሪቱ ሰላም አሰፍናለሁ፤+ እናንተም ማንም ሳያስፈራችሁ ትተኛላችሁ፤+ እኔም አደገኛ አውሬዎች በምድሪቱ እንዳይኖሩ አደርጋለሁ፤ በምድራችሁም የጦርነት ሰይፍ አያልፍም። 7 እናንተም በእርግጥ ጠላቶቻችሁን ታሳድዳላችሁ፤ እነሱም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ። 8 አምስታችሁ 100 ሰዎችን ታሳድዳላችሁ፤ መቶዎቻችሁ ደግሞ 10,000 ሰዎችን ታሳድዳላችሁ፤ ጠላቶቻችሁም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።+
9 “‘እኔም ሞገስ አሳያችኋለሁ፤* ፍሬያማ እንድትሆኑና እንድትበዙ አደርጋችኋለሁ፤+ ከእናንተ ጋር የገባሁትንም ቃል ኪዳኔን እጠብቃለሁ።+ 10 እናንተም ያለፈውን ዓመት እህል ገና በልታችሁ ሳትጨርሱ ለዘንድሮው እህል ቦታ ለማግኘት ያለፈውን ዓመት እህል ታስለቅቃላችሁ። 11 የማደሪያ ድንኳኔን በመካከላችሁ እተክላለሁ፤+ እኔም አልተዋችሁም።* 12 በመካከላችሁ እሄዳለሁ፤ አምላካችሁም እሆናለሁ፤+ እናንተ ደግሞ ሕዝቦቼ ትሆናላችሁ።+
-