9 በተጨማሪም አምላክ አብርሃምን እንዲህ አለው፦ “በአንተ በኩል፣ አንተም ሆንክ ከአንተ በኋላ የሚመጡት ዘሮችህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ቃል ኪዳኔን መጠበቅ አለባችሁ። 10 እናንተም ሆናችሁ ከእናንተ በኋላ የሚመጡት ዘሮቻችሁ ልትጠብቁት የሚገባው በእኔና በእናንተ መካከል ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው፦ በእናንተ መካከል ያለ ወንድ ሁሉ መገረዝ አለበት።+ 11 ሸለፈታችሁን መገረዝ አለባችሁ፤ ይህም በእኔና በእናንተ መካከል ላለው ቃል ኪዳን እንደ ምልክት ሆኖ ያገለግላል።+