-
ዘኁልቁ 10:29-32አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
29 ከዚያም ሙሴ የአማቱን የምድያማዊውን የረኡዔልን*+ ልጅ ሆባብን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ እኛ ይሖዋ ‘ለእናንተ እሰጣችኋለሁ’+ ወዳለን ምድር ተነስተን መጓዛችን ነው። አንተም ከእኛ ጋር ና፤+ ይሖዋ ለእስራኤል መልካም ነገር ለማድረግ ቃል ስለገባ+ እኛም መልካም ነገር እናደርግልሃለን።” 30 እሱ ግን “አብሬያችሁ አልሄድም። እኔ ወደ አገሬና ወደ ዘመዶቼ እመለሳለሁ” አለው። 31 በዚህ ጊዜ እንዲህ አለው፦ “በምድረ በዳው የት መስፈር እንዳለብን ስለምታውቅ እባክህ ትተኸን አትሂድ፤ መንገድም ልትመራን* ትችላለህ። 32 ከእኛ ጋር የምትሄድ ከሆነ+ ይሖዋ የሚያደርግልንን መልካም ነገር ሁሉ እኛም በእርግጥ ለአንተ እናደርግልሃለን።”
-