11 በይሳኮርና በአሴር ግዛቶች ውስጥ ለምናሴ የተሰጡት የሚከተሉት ናቸው፦ ቤትሼንና በሥሯ ያሉት ከተሞች፣ ይብለአምና+ በሥሯ ያሉት ከተሞች፣ የዶር+ ነዋሪዎችና በሥሯ ያሉት ከተሞች እንዲሁም የኤንዶር+ ነዋሪዎችና በሥሯ ያሉት ከተሞች፣ የታአናክ+ ነዋሪዎችና በሥሯ ያሉት ከተሞች፣ የመጊዶ ነዋሪዎችና በሥሯ ያሉት ከተሞች፣ ሦስቱ ኮረብታማ አካባቢዎች።
12 ሆኖም የምናሴ ዘሮች እነዚህን ከተሞች መውረስ አልቻሉም፤ ከነአናውያን ይህን ምድር ላለመልቀቅ ቆርጠው ነበር።+