-
ዘኁልቁ 21:21-26አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 እስራኤላውያን የአሞራውያን ንጉሥ ወደሆነው ወደ ሲሖን እንዲህ በማለት መልእክተኞችን ላኩ፦+ 22 “ምድርህን አቋርጠን እንድናልፍ ፍቀድልን። ወደ የትኛውም እርሻ ወይም ወደ የትኛውም የወይን ቦታ አንገባም። ከየትኛውም ጉድጓድ ውኃ አንጠጣም። ክልልህን አቋርጠን እስክናልፍ ድረስ በንጉሡ መንገድ ቀጥ ብለን እንሄዳለን።”+ 23 ሲሖን ግን እስራኤላውያን ክልሉን አቋርጠው እንዲያልፉ አልፈቀደላቸውም። ከዚህ ይልቅ ሲሖን ሕዝቡን ሁሉ ሰብስቦ እስራኤልን ለመውጋት ወደ ምድረ በዳው ሄደ፤ ያሃጽ በደረሰ ጊዜም ከእስራኤላውያን ጋር ውጊያ ገጠመ።+ 24 እስራኤላውያን ግን በሰይፍ ድል አደረጉት፤+ ምድሩንም ከአርኖን+ አንስቶ በአሞናውያን አቅራቢያ እስከሚገኘው እስከ ያቦቅ+ ድረስ ያዙ፤+ ሆኖም ያዜር+ የአሞናውያን ወሰን+ ስለሆነ ከዚያ አላለፉም።
25 በመሆኑም እስራኤላውያን እነዚህን ከተሞች ሁሉ ያዙ፤ ከዚያም በአሞራውያን+ ከተሞች ይኸውም በሃሽቦንና በሥሯ* ባሉት ከተሞች ሁሉ መኖር ጀመሩ። 26 ምክንያቱም ሃሽቦን የአሞራውያን ንጉሥ የሲሖን ከተማ ነበረች፤ እሱም ከሞዓብ ንጉሥ ጋር ተዋግቶ እስከ አርኖን ድረስ ያለውን ምድር ከእጁ ወስዶበት ነበር።
-