ዘፍጥረት 49:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 “ከእስራኤል ነገዶች አንዱ የሆነው ዳን+ በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል።+ መሳፍንት 2:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 በመሆኑም ይሖዋ ከዘራፊዎቻቸው እጅ የሚያድኗቸውን መሳፍንት አስነሳላቸው።+ መሳፍንት 13:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 እስራኤላውያን እንደገና በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር አደረጉ፤+ ይሖዋም ለ40 ዓመት በፍልስጤማውያን እጅ አሳልፎ ሰጣቸው።+ መሳፍንት 13:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 እነሆ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ይህ ልጅ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ* የአምላክ ናዝራዊ* ስለሚሆን ራሱን ምላጭ አይንካው፤+ እሱም እስራኤልን ከፍልስጤማውያን እጅ በማዳን ረገድ ግንባር ቀደም ይሆናል።”+ መሳፍንት 16:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 በኋላም ወንድሞቹና የአባቱ ቤተሰቦች በሙሉ ሊወስዱት ወደዚያ ወረዱ። እነሱም ወስደው በጾራ+ እና በኤሽታዖል መካከል በሚገኘው በአባቱ በማኑሄ+ የመቃብር ስፍራ ቀበሩት። እሱም በእስራኤል ውስጥ ለ20 ዓመት ፈራጅ ሆኖ አገለገለ።+ ዕብራውያን 11:32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 እንግዲህ ከዚህ በላይ ምን እላለሁ? ስለ ጌድዮን፣+ ስለ ባርቅ፣+ ስለ ሳምሶን፣+ ስለ ዮፍታሔ፣+ ስለ ዳዊት+ እንዲሁም ስለ ሳሙኤልና+ ስለ ሌሎቹ ነቢያት እንዳልተርክ ጊዜ ያጥረኛል።
5 እነሆ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ይህ ልጅ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ* የአምላክ ናዝራዊ* ስለሚሆን ራሱን ምላጭ አይንካው፤+ እሱም እስራኤልን ከፍልስጤማውያን እጅ በማዳን ረገድ ግንባር ቀደም ይሆናል።”+
31 በኋላም ወንድሞቹና የአባቱ ቤተሰቦች በሙሉ ሊወስዱት ወደዚያ ወረዱ። እነሱም ወስደው በጾራ+ እና በኤሽታዖል መካከል በሚገኘው በአባቱ በማኑሄ+ የመቃብር ስፍራ ቀበሩት። እሱም በእስራኤል ውስጥ ለ20 ዓመት ፈራጅ ሆኖ አገለገለ።+
32 እንግዲህ ከዚህ በላይ ምን እላለሁ? ስለ ጌድዮን፣+ ስለ ባርቅ፣+ ስለ ሳምሶን፣+ ስለ ዮፍታሔ፣+ ስለ ዳዊት+ እንዲሁም ስለ ሳሙኤልና+ ስለ ሌሎቹ ነቢያት እንዳልተርክ ጊዜ ያጥረኛል።