ኢያሱ 19:47, 48 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 47 የዳን ዘሮች ርስታቸው በጣም ጠቧቸው ነበር።+ በመሆኑም ወጥተው ለሸምን+ ወጉ፤ ከተማዋንም በመቆጣጠር በሰይፍ መቷት። ከዚያም ከተማዋን ርስት አድርገው በመያዝ በዚያ መኖር ጀመሩ፤ ለሸምንም በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሯት።+ 48 የዳን ነገድ ርስት በየቤተሰቡ ይህ ነበር። ከተሞቹና መንደሮቻቸው እነዚህ ነበሩ። መሳፍንት 1:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 ዳናውያን ወደ ሜዳው* እንዲወርዱ አሞራውያን ስላልፈቀዱላቸው በተራራማው አካባቢ ተወስነው ለመኖር ተገደዱ።+
47 የዳን ዘሮች ርስታቸው በጣም ጠቧቸው ነበር።+ በመሆኑም ወጥተው ለሸምን+ ወጉ፤ ከተማዋንም በመቆጣጠር በሰይፍ መቷት። ከዚያም ከተማዋን ርስት አድርገው በመያዝ በዚያ መኖር ጀመሩ፤ ለሸምንም በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሯት።+ 48 የዳን ነገድ ርስት በየቤተሰቡ ይህ ነበር። ከተሞቹና መንደሮቻቸው እነዚህ ነበሩ።