ዘፍጥረት 30:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ራሔልም “አምላክ ዳኛ ሆነልኝ፤ ቃሌንም ሰማ። በመሆኑም ወንድ ልጅ ሰጠኝ” አለች። በዚህም የተነሳ ስሙን ዳን*+ አለችው። ዘፍጥረት 32:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ሰውየውም “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል* እንጂ ያዕቆብ አይባልም፤+ ምክንያቱም ከአምላክም ሆነ ከሰዎች ጋር ታግለህ+ በመጨረሻ አሸንፈሃል” አለው።